Mégsem tetszik a termék? Semmi gond! Nálunk 30 napon belül visszaküldheti
Ajándékutalvánnyal nem hibázhat. A megajándékozott az ajándékutalványért bármit választhat kínálatunkból.
30 nap a termék visszaküldésére
ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ለዚህ ዘመን ትውልድ ብዙ ስንቅ የያዘ ነው፡፡ ስንቁም በመንፈሳዊነት የሚሰግድ የገንዘብ ሚኒስትር የሆነ ባለ ሥልጣን ፣ ሀገር አቋራጭ ተሳላሚ ባለጸጋ ፣ ከስግደት መልስ የሚያነብ ትጉሕ አንባቢ ፣ ጎበዝ ጠያቂና ተማሪ ፣ እነሆ ውኃ ብሎ ከችግር በፊት መፍትሔ አቅራቢ ፣ የሚከለክለኝ ምንድን ነው ብሎ ችግሩን ከሥር ፈላጊ ፣ እምነቱን ለመግለጽ የማያፍር መስካሪ ፣ ወዲያው ወስኖ ለጥምቀት የሚበቃ አማኝ የሆነ ሰው ለዚህ ትውልድ ትልቅ ሐዋርያ ነው፡፡ የጃንደረባው መንፈስ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድን ወለደ፡፡ ኢጃት ምን እንደሚወልድ ደግሞ ዕድሜ የሠጠው ሰው የሚያየው ይሆናል፡፡ ይህን ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ የተሰኘ መጽሐፍ የጃንደረባውን መንፈስ ለሚከተሉ ማስታወሻ ይሆን ዘንድ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ አበርክቻለሁ፡፡ በጸሎታችሁ አስቡኝ፡፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ